ማን ነው የፈጠረኝ? ለምንስ ፈጠረኝ?ሁሉም ነገር ፈጣሪ እንዳለ ይጠቁማል
ይህንን ትምህርት ወደ ሚከተለው ቋንቋ ተቶርግሟል
- English - English
- български - Bulgarian
- português - Portuguese
- svenska - Swedish
- العربية - Arabic
- Wikang Tagalog - Tagalog
- Kurdî - Kurdish
- Français - French
- हिन्दी - Hindi
- español - Spanish
- čeština - Czech
- Русский - Russian
- Bahasa Indonesia - Indonesian
- ગુજરાતી - Unnamed
- অসমীয়া - Assamese
- ไทย - Thai
- Deutsch - German
- Tiếng Việt - Vietnamese
- italiano - Italian
- فارسی دری - Unnamed
- বাংলা - Bengali
- Shqip - Albanian
- 中文 - Chinese
- Nederlands - Dutch
- Kiswahili - Swahili
- اردو - Urdu
- Hausa - Hausa
- پښتو - Pashto
- සිංහල - Sinhala
- magyar - Hungarian
- ქართული - Georgian
- bamanankan - Bambara
- Akan - Akan
- Lingala - Unnamed
- ئۇيغۇرچە - Uyghur
- bosanski - Bosnian
ምድቦች
Full Description
ማን ነው የፈጠረኝ? ለምንስ ፈጠረኝ?ሁሉም ነገር ፈጣሪ እንዳለ ይጠቁማል
ሰማያትንና ምድርን፣ በውስጣቸውም ያለውን ማንም ሊያካብባቸው የማይቻሉ የሆኑትን ትላልቅ ፍጡራንን የፈጠራቸው ማን ነው?
ይህን በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ፍፁም የረቀቀ የሆነውን ስርዓት የዘረጋው ማን ነው?
የሰውን ልጅ መስሚያ፣ መመልከቻና አዕምሮ ለግሶ፤ ዕውቀትን በመፈለግ እውነታ ላይ እንዲደርስ ያስቻለውስ ማን ነው?
ይህንን በሰውነትዎም በሕያዋን ፍጥረታት አካላትም ውስጥ ያለውን ይህንን የረቀቀ አሠራር እንዴት ይገልፁታል!? ማንስ ፈጠረው?
ይህ ታላቅ አጽናፈ ዓለም ረቂቅ በሆነ መልኩ የሚቆጣጠረውን ስርዓት ይዞ እንዴት ለዚህ ሁሉ ዓመታት ወጥ እና የተረጋጋ ሊሆን ቻለ?
ይህን ዓለም የሚገዙትን ሥርዓቶች (ሕይወትና ሞትን፣ የሕያዋን መባዛት፣ ቀንና ሌሊት፣ የወቅቶች መለዋወጥ ወዘተ) ማን ነው ያስቀመጠው?
ይህ ፍጥረተ ዓለም ራሱን ፈጠረ? ወይስ ያላንዳች ነገር በራሱ መጣ? ወይንስ እንዲሁ ባጋጣሚ ተከሰተ?
የሰው ልጅ የማያያቸው ነገሮችም መኖራቸውን የሚያምነው ለምንድን ነው? ለምሳሌ:- (ማወቅ፣ አይምሮ፣ ነፍስ፣ ስሜት፣ ፍቅር) ተፅእኗቸውን ስለሚያይ አይደለምን? ታዲያ የሰው ልጅ የፍጡራኑን፣ የስራዎቹንና የእዝነቱን ተጽእኖ ምድር ላይ እያየም እንዴት የዚህን ታላቅ አጽናፈ ዓለም ፈጣሪ መኖርን ይክዳል?
«ይህ ቤት ማንም ሳይሰራው እንዲሁ የመጣ ነው።» ቢባል፤ ወይም ደግሞ «ይህንን ቤት ህልውና የሰጠው ህልውና የሌለው ነገር ነው።» የሚልን አስተሳሰብ ማንም አይቀበለውም። ታዲያ አንዳንድ ሰዎች «ይህ ታላቁ ዓለም ያለ ፈጣሪ የተገኘ ነው።» ሲባሉ አምነው የሚቀበሉት ለምን ይሆን?! አዕምሮ ያለው ሰው «ይህ ረቂቅ የሆነው የዓለም ስርዓት እንዲሁ ባጋጣሚ የመጣ ነው።» ሲባል እንዴት ይቀበለዋል?!
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:(أَمۡ خُلِقُواْ مِنۡ غَيۡرِ شَيۡءٍ أَمۡ هُمُ ٱلۡخَٰلِقُونَ، أَمۡ خَلَقُواْ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَۚ بَل لَّا يُوقِنُونَ). {ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም።}[32 : 52]
ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው አላህ ነው።
ያለው አንድ ጌታና ፈጣሪ ነው። ለርሱም ምሉዕነቱን የሚጠቁሙ ትላልቅና በርካታ ስሞችና ባህሪያት አሉት። ከስሞቹም መካከል: "አል‐ኻሊቅ" (ፈጣሪ)፣ "አር‐ረሒም" (አዛኝ)፣ "አር‐ረዛቅ" (ለጋሽ)፣ "አል‐ከሪም" (ቸር) እና "አላህ" የሚባሉትን መጥቀስ የሚቻል ሲሆን ጥራት ከተገባው ጌታ ስሞች መካከል እጅግ አንጋፋው ስሙ አላህ የሚለው ነው። ትርጉሙም: በብቸኝነት ለአምልኮ የተገባና አጋር የሌለው ማለት ነው።
የላቀው አላህ በተከበረው ቁርአን እንዲህ ብሏል:﴿قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ {በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ [1]* ٱللَّهُ ٱلصَّمَدُ *አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡*لَمۡ یَلِدۡ وَلَمۡ یُولَدۡ *አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡*وَلَمۡ یَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدُۢ﴾ *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»}[112 : 1-4]
አላህ እንዲህም ብሏል:﴿اللَّهُ لا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلا نَوْمٌ لَهُ مَا فِي السَّمَوَاتِ وَمَا فِي الأَرْضِ مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ وَلا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ﴾ {አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡}[2 : 255]
ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው ጌታ ያሉት ባህሪያት
እርሱም ምድርን የፈጠረና ያገራት፤ ለፍጡራኑም የምትመች ያደረጋት፤ ሰማያትንና በውስጧ ያሉትን ትላልቅ ፍጡራን የፈጠረ፤ ለፀሀይ፣ ለጨረቃ፣ ለምሽትና ለቀን ይህን ታላቅነቱን የሚጠቁም የረቀቀ ስርዓት የዘረጋ ጌታ ነው።
እርሱም ለኛ ያለርሱ ህይወት የሌለንን አየርን ያገራልን፤ በኛ ላይ ዝናቦችን ያወረደልን፤ ወንዞችና ውቅያኖሶችን ያገራልን፤ ምንም አቅም ባልነበረን በናቶቻችን ሆድ ውስጥ ፅንስ በነበርንበት ወቅትም ሲቀልበን የነበረ፤ ከውልደታችን ጀምሮ እስከምንሞት ድረስ በደም ስሮቻችን ደምን ያዘዋወረልንና ልቦቻችን ሳያቋርጥ እንዲመታ ያደረገልን ጌታ ነው።
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:﴿وَاللَّهُ أَخْرَجَكُمْ مِنْ بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ﴾ {አላህም ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ፡፡}(16፡ 78)
የምናመልከው ጌታችን መገለጫዎቹ የግድ ምሉዕ ባህሪ ሊሆኑ ይገባል።
ፈጣሪያችን ታላቅነቱን የምንገነዘብበትን አዕምሮ ሰጠን፤ ምሉዕነቱንም የሚያመለክተን ተፈጥሮ በውስጣችን አኖረ፤ በጉድለትም በፍፁም ሊገለፅ አይችልም።
አምልኮ የግድ ለአላህ ብቻ ሊሆን ይገባል። ምሉዕና ለአምልኮ የተገባውም እርሱ ነው። ከርሱ ውጪ የሚመለኩ ሁሉ ከንቱና ጎዶሎ፣ ለጥፋትና ለሞትም የተጋረጡ ናቸው።
ሰው፣ ጣዖት፣ ዛፍና እንስሳ በፍፁም አምላክ ሊሆኑ አይችሉም።
አንድ ጤነኛ አይምሮ ያለው ሰው ምሉዕ ከሆነው አምላክ ውጪ ማምለክ አይገባውም። እንዴት ከርሱ በታች የሆነን ፍጡር ያመልካል?
ጌታ በሴት ማህፀን ውስጥ ሊፀነስና እንደማንኛውም ህፃን የተወለደ ሊሆን አይችልም።
ጌታ ፍጡራንን የፈጠረ፤ ፍጡራንም በጭብጡና በኃይሉ ስር በመሆናቸው ሰው ሊጎዳውም አይችልም። አንድም አካል ሊሰቅለውም፣ ሊቀጣውም፣ ሊያዋርደውም አይችልም።
የሚሞት አካል ጌታ ሊሆን አይችልም።
ጌታ የማይረሳ፣ የማይተኛ፣ ምግብ የማይበላ፣ ሚስትና ልጅ ሊኖረው የማይገባ ታላቅ ነው። ፈጣሪ የታላቅነት መገለጫዎች አሉት። በፈላጊነትም ይሁን በጉድለት የማይገለፅ ፍፁም ሲሆን፤ ነቢያቶች ተናግረውታል ተብሎ ወደ ነቢያቶች የሚላከኩ የፈጣሪን ታላቅነት የሚጻረር ሀሳብ የያዙ ጥቅሶች ሁሉ የተጣመሙ ጽሑፎች እንጂ ሙሳ፣ ዒሳ አልያም ሌሎች ነብያት (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) ካመጡት ከትክክለኛው ራዕይ የተወሰዱ አይደሉም።
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَنْ يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ وَإِنْ يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَا يَسْتَنْقِذُوهُ مِنْهُ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ (73) እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም እንኳን (አይችሉም)፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡ (73)مَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ (74) አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ አላህ በጣም ኃያል አሸናፊ ነው፡፡ (74)[22: 73,74]
ፈጣሪ ያለ መለኮታዊ ራዕይ ሊተወን ይችላል ተብሎ ይታሰባል?
አላህ እነዚህን ሁሉ ፍጥረታት ያለ አላማ ነው የፈጠራቸው ተብሎስ ይታሰባልን? እርሱ ጥበበኛና አዋቂ ሆኖ ሳለ ለጨዋታ ይፈጥራቸዋልን?
እንዲህ ባለ ወጥ ፍፁምነት የፈጠረን በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ያስገዛልን ያለ ዓላማ ሊፈጥረን ይችላል ተብሎ ይታሰባልን? ወይስ ለምንድነው እዚህ አለም ላይ ያለነው? ከሞት በኋላ ምንድነው ያለው? የመፈጠራችን አላማስ ምንድን ነው? የመሳሰሉ እኛን እጅግ የጠመዱንን አንገብጋቢ ጥያቄዎች ሳይመልስ ሊተወን ይችላልን?
ይልቁንም የመፈጠራችንን አላማና ከኛ ምን እንደሚጠበቅብን እንድናውቅ ነው አላህ መልክተኞችን የላከው።
አላህ መልእክተኞቹን የላከው እርሱ ብቻ ለአምልኮ የተገባ እንደሆነ ሊነግሩን፤ እንዴት እንደምናመልከው እንድናውቅ፤ ትእዛዙንና ክልከላውንም ሊያደርሱን፤ እርሷን ከያዝን ህይወታችን ምርጥ የምትሆንበትን፣ መልካምና በረከት የሚያካብበንን በላጭና ቀጥ ያለ እውቀት እንዲያስተምሩን ነው።
አላህ በርካታ መልክተኞችን ልኳል። ለምሳሌ (ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳና ዒሳ) ይገኛሉ። ለነዚህም መልክተኞች እውነተኝነታቸውንና ከፈጣሪ ዘንድ የተላኩ መልክተኞች መሆናቸውን የሚጠቁሙ ተአምራትንም አላህ ሰጥቷቸዋል።
የመጨረሻው መልክተኛም ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ናቸው። በርሳቸውም ላይ የተከበረውን ቁርአን አወረደ።
መልክተኞች ፍንትው ባለ መልኩ ይህ ህይወት የፈተና ህይወት መሆኑንና ትክክለኛውም ህይወት ከሞት በኋላ መሆኑን ነግረውናል።
በመጪው ዓለምም በአላህ ላይ ምንንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ላመለኩት በሁሉም መልክተኞችም ላመኑ አማኞች ጀነት እንዳለ፤ እንዲሁም ከአላህ ጋር ሌላ አማልክትን ላመለኩ ወይም ከአላህ መልክተኞች መካከል በማንኛውም መልክተኛ ለካዱ ከሀዲያንም አላህ እሳትን እንዳዘጋጀ ነግረውናል።
ከፍ ያለው አላህ አለ:
يَابَنِي آدَمَ إِمَّا يَأْتِيَنَّكُمْ رُسُلٌ مِنْكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي فَمَنِ اتَّقَى وَأَصْلَحَ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ (35) «የአዳም ልጆች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ በናንተ ላይ አንቀጾቼን የሚያነቡ መልከተኞች ቢመጧችሁ ከእናንተ ክሕደትን የተጠነቀቁና መልካምንም የሠሩ በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነሱም አያዝኑም፡፡ (35)وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا وَاسْتَكْبَرُوا عَنْهَا أُولَئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ (36) «እነዚያም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ (36)»[7 : 35,36]
አላህ -ጥራት ይገባውና- እንዲህም ብሏል፦﴿ أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ ﴾ «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መሆኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መሆናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)[23 : 115]
የተከበረው ቁርኣን
የተከበረው ቁርኣን አላህ በመጨረሻ መልክተኛው ሙሐመድ ላይ ያወረደው ቃሉ ሲሆን የሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት እውነተኝነትን የሚያመለክት ትልቁ ተአምር ነው። በህግጋቶቹ ትክክልና በንግግሮቹም እውነተኛ ነው። አላህ ከሓዲዎች እንደዚች ቁርኣን አምሳያ አንዲት ምዕራፍ እንኳ እንዲያመጡ ተገዳድሯቸዋል። ነገር ግን ከንግግር ውበቱ እና ከቃላቱ ምጥቀት አንፃር አምሳያውን ሊያመጡ አልቻሉም። ይህ መጽሐፍ በሰዎች የተፈበረከ ሳይሆን ጥራት የተገባው የሰው ልጅ ጌታ ንግግር መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ አእምሯዊ አመክንዮዎችን እና ሳይንሳዊ እውነታዎችን አካትቷል።
ብዙ መልክተኞች የተላኩበት ምክንያት ምንድን ነው?
አላህ ከጥንት ጀምሮ ሰዎችን ወደ ጌታቸው እንዲጠሩ፣ ትእዛዙንና ክልከላዎቹንም ለነርሱ እንዲያደርሱ መልእክተኞችን ልኳል። የሁሉም ጥሪም፡- አላህን ዐዘ ወጀል ብቻ እንዲገዙ መጣራት ነበር። አንድ ህዝብ መልክተኛቸው ያመጣውን ወደ አላህ አሃዳዊነት የመጣራት ጥሪ ችላ ማለት ወይም ማዛባት በጀመሩ ቁጥር መንገዱን እንዲያስተካክልና አላህን በመነጠልና በመታዘዝ ሰዎችን ወደ ንፁህ ተፈጥሯቸው እንዲመልስ ሌላን መልእክተኛ ይመድባል። ይህም አላህ መልክተኞችን በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስኪደመድም ድረስ ቀጥሏል። እርሳቸውም ለሰው ዘር ባጠቃላይ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የምትዘወትርን፣ ያለፉትን ድንጋጌዎችም የምትሽርና የምታሟላ ድንጋጌ ይዘው መጡ። ጌታችንም ይህች ድንጋጌና ተልእኮ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የምትዘልቅ መሆኗን ኃላፊነቱን ወስዷል።
ስለዚህም እኛ ሙስሊሞች አላህ ባዘዘን መልኩ በሁሉም መልክተኞችና በቀደሙ መጽሐፍት እናምናለን።
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:﴿ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَاۤ أُنزِلَ إِلَیۡهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَـٰۤىِٕكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَیۡنَ أَحَدࣲ مِّن رُّسُلِهِۦۚ وَقَالُوا۟ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَاۖ غُفۡرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَیۡكَ ٱلۡمَصِیرُ﴾ {መልክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ። ምእመኖቹም (እንደዚሁ)። ሁሉም በአላህ፣ በመላእክቱም፣ በመፃህፍቱም፣ በመልክተኞቹም፣ ከመልክተኞቹ "በአንድም መካከል አንለይም።" (የሚሉ ሲሆኑ) አመኑ። "ሰማን ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ ምህረትህን (እንሻለን)። መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው።" አሉም።}[2: 285]. [2 : 285]
ማንኛውም ግለሰብ በሁሉም መልክተኞች ካላመነ አማኝ አይሆንም።
መልክተኞችን የላከው አሏህ ነው። ከነዚህ መልክተኞች መካከል በአንዱ መልክተኝነት የካደ ሰው በሁሉም ክዷል። ሰው የአላህን መለኮታዊ ራዕይ ከመመለስ የባሰ ወንጀል የለውም። ስለሆነም ጀነት ለመግባት በመልክተኞች ባጠቃላይ ማመን ግዴታ ነው።
በዚህ ዘመን በእያንዳንዱ ላይ ያለበት ግዴታ በአላህ መልክተኞች ባጠቃላይ ማመን ነው። ይህም የመጨረሻውና የነቢያት መደምደሚያ በሆኑት ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በማመንና እሳቸውን በመከተል ካልሆነ በቀር እውን አይሆንም።
አላህ በተከበረው ቁርአን ውስጥ ከአላህ መልክተኞች መካከል በማንኛውም መልክተኛ ማመንን የማይቀበል ሰው በአላህ የካደና መለኮታዊ ራዕዩን አስተባባይ እንደሆነ ጠቅሷል።
የሚከተለውን አንቀፅ አንብብ:"إنَّ الَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِاللَّهِ ورُسُلِهِ ويُرِيدُونَ أنْ يُفَرِّقُوا بَيْنَ اللَّهِ ورُسُلِهِ ويَقُولُونَ نُؤْمِنُ بِبَعْضٍ ونَكْفُرُ بِبَعْضٍ ويُرِيدُونَ أنْ يَتَّخِذُوا بَيْنَ ذَلِكَ سَبِيلًا እነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ የሚክዱ፣ በአላህና በመልክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉ፣ «በከፊሉም እናምናለን በከፊሉም እንክዳለን» የሚሉ፣ በዚህም መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፤أُولَئِكَ هُمُ الكافِرُونَ حَقًّا وأعْتَدْنا لِلْكَفَرَيْنِ عَذابًا مُهِينًا﴾". እነዚያ በውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ ለከሓዲዎችም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል፡፡}[4 : 150,151]
እስልምና ምንድን ነው?
እስልምና ማለት ለአላህ በብቸኝነት እጅ መስጠት፤ ለትእዛዙ ታዛዥ መሆን፤ ድንጋጌውንም በውዴታና በመቀበል መተግበር ማለት ነው።
አላህ መልክተኞችን ለአንድ ተልዕኮ ነው የላካቸው። እርሱም: ምንም ሳያጋሩበት በብቸኝነት ወደ አላህ አምልኮ እንዲጣሩ ነው።
እስልምና የነብያት ሁሉ ሃይማኖት ነው። ነቢያቶች ዝርዝር ህግጋታቸው ቢለያይም ጥሪያቸው አንድ ነው። ዛሬ ላይ ሁሉም ነብያት ያመጡትን ትክክለኛ ሀይማኖት አጥብቀው የያዙት ሙስሊሞች ብቻ ናቸው። በዚህ ሰአት የእስልምና መልእክት ብቸኛው እውነት ነው። ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳን የላከው ጌታ የመጨረሻውንም መልእክተኛ መሐመድን የላከው ጌታ ነው። የእስልምና ድንጋጌም ከሱ በፊት የነበሩትን ድንጋጌዎች ሻሪ ሆኖ ነው የመጣው።
በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሚያምኗቸው ሃይማኖቶች - ከእስልምና በቀር - በሰዎች የተሠሩ ሃይማኖቶች ወይም መለኮታዊ የነበሩ ከዚያም በሰው እጅ የተጨማለቁ የእንቶፈንቶ፣ የተወረሱ አፈ ታሪኮች እና የሰው ስሪት ድብልቅና ጥርቅም የሆኑ ሃይማኖቶች ናቸው። የሙስሊሞች እምነት ግን የማይለወጥ አንድ ግልጽ እምነት ነው። ቅዱስ ቁርኣንን ተመልከት በሁሉም የሙስሊም ሀገራት አንድ መጽሐፍ ነው።
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በቁርአን ውስጥ እንዲህ ብሏል:
قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنْزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنْزِلَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَى وَعِيسَى وَالنَّبِيُّونَ مِنْ رَبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ (84) «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም (በቁርኣን)፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ በተወረደው፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው (አመንን)፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ (84)وَمَنْ يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَنْ يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ 85). ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ (85)[3 : 84,85]
ሙስሊሞች በኢየሱስ (የአላህ ሰላም ይስፈንበትና) ዙሪያ ምንድን ነው የሚያምኑት?
ሙስሊሞች የአላህን ነቢይ ኢየሱስን በነቢይነቱ የማመን፣ የመውደድ፣ የማክበር እና አላህን ብቻ ያለ አጋር እንዲመለክ ያደረጉትን ጥሪ የማመን ግዴታ እንዳለባቸው ታውቃለህ? ሙስሊሞች ነቢዩ ኢሳም ይሁን ነብዩ ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርነርሱ ላይ ይስፈንና) ነብይ እንደነበሩ እና ሰዎችንም ወደ አላህ መንገድ እና ወደ ጀነት መንገድ እንዲመሩ የተላኩ ናቸው ብለው ያምናሉ።
ዒሳ የአላህ ሰላም ይስፈንባቸውና አላህ ከላካቸው ታላላቅ መልእክተኞች መካከል አንዱ መሆናቸውን እናምናለን። ተአምራዊ በሆነ መልኩ መወለዳቸውንም እናምናለን። አላህም በቁርኣን ውስጥ አደምን አባትና እናት ሳይኖረው እንደፈጠረው ሁሉ ዒሳንም ያለ አባት እንደፈጠረው ነግሮናል ። ይህም አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ስለሆነ ነው።
ዒሳ አምላክም እንዳልሆኑ፤ የአላህም ልጅ እንዳልሆኑ እናምናለን። አልተሰቀሉምም ይልቁንም አላህ በመጨረሻው ዘመን ፍትሀዊና ፈራጅ አድርጎ ሊያወርዳቸውው ወደራሱ አነሳቸው። ሲመጡም ከሙስሊሞች ጋር ነው የሚሆኑት። ምክንያቱም ዒሳና ሁሉም ነቢያት ይዘውት የመጡትን ተውሒድ የሚያምኑት ሙስሊሞች ናቸውና።
አላህ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የዒሳ ተልእኮ በክርስቲያኖች እንደተበረዘ እና ኢንጂልን ያጣመሙትና የቀየሩት እንዲሁም ዒሳ ያልተናገራቸውን ጥቅሶች የጨመሩ የተሳሳቱ ጠማሞች እንዳሉ ገልጾልናል። የኢንጂል ቅጂ መበርከቱና በውስጡም እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ በርካታ ጥቅሶች መኖራቸው ለዚህ ማረጋገጫ ነው።
ዒሳ ጌታውን የሚያመልክ ነበር እንጂ እንዲያመልኩት ማንንም እንዳልጠየቀ አላህ ነግሮናል። ይልቁንም ህዝቦቹ ፈጣሪውን እንዲያመልኩ ያዝ ነበር። ሰይጣን ግን ክርስቲያኖች ኢየሱስን እንዲያመልኩት አደረገ። አላህም በቁርኣን ላይ ከአላህ ሌላ ያመለከን ሰው ይቅር እንደማይል ዒሳም በትንሳኤ ቀን ከእነዚያ ካመለኩት እንደሚጥራራ፣ ለነርሱም "እኔ ፈጣሪን እንድትገዙ አዝዣችኋለሁ እንጂ እንድትገዙኝ አልጠየኳችሁም።" እንደሚል ነግሮናል። ለዚህም ማስረጃው ይህ የአላህ ንግግር ነው:
﴿یَـٰۤأَهۡلَ ٱلۡكِتَـٰبِ لَا تَغۡلُوا۟ فِی دِینِكُمۡ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡحَقَّۚ إِنَّمَا ٱلۡمَسِیحُ عِیسَى ٱبۡنُ مَرۡیَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥۤ أَلۡقَىٰهَاۤ إِلَىٰ مَرۡیَمَ وَرُوحࣱ مِّنۡهُۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَـٰثَةٌۚ ٱنتَهُوا۟ خَیۡرࣰا لَّكُمۡۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَـٰهࣱ وَ ٰحِدࣱۖ سُبۡحَـٰنَهُۥۤ أَن یَكُونَ لَهُۥ وَلَدࣱۘ لَّهُۥ مَا فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰتِ وَمَا فِی ٱلۡأَرۡضِۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِیلࣰا﴾ {እናንተ የመፅሀፍ ሰዎች ሆይ! በሀይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ። በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ። የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት የ "ሁን" ቃሉም ከእርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው። በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ። "(አማልክት) ሶስት ናቸው" አትበሉም። ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይሆናልና። አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው። ለእርሱ ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው። በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው። መመኪያም በአላህ በቃ።}[4: 171]
አላህ እንዲህ ብሏል፡(وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ قَالَ سُبْحَانَكَ مَا يَكُونُ لِي أَنْ أَقُولَ مَا لَيْسَ لِي بِحَقٍّ ۚ إِن كُنتُ قُلْتُهُ فَقَدْ عَلِمْتَهُ ۚ تَعْلَمُ مَا فِي نَفْسِي وَلَا أَعْلَمُ مَا فِي نَفْسِكَ ۚ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ (አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብላሃልን» በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ጥራት ይገባህ፤ ለእኔ ተገቢዬ ያልኾነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደ ኾነም በእርግጥ ዐውቀኸዋል፡፡ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ግን አንተ ዘንድ ያለውን አላውቅም፡፡ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና» ይላል፡፡(5: 116)
በመጪው ዓለም ለመዳን የሚፈልግ ሰው እስልምናን ተቀብሎ ነቢዩ ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መከተል ይኖርበታል።
ሁሉም ነብያትና መልእክተኞች (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) ከተስማሙባቸው እውነታዎች አንዱ በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ አምነው፣ ማንንም በርሱ ላይ በአምልኮ ሳያጋሩ፣ በነቢያትና በመልእክተኞች ሁሉ ያመኑ ሙስሊሞች ካልሆኑ በቀር ማንም በመጪው ዓለም የማይድን መሆኑን ነው። በነብዩ ሙሳ ጊዜ የነበሩት እና በእርሱ አምነው አስተምህሮቱንም የተከተሉ እነርሱ ደጋግ ሙስሊሞች እና አማኞች ናቸው። ነገር ግን አላህ ዒሳን ከላከ በኋላ የሙሳ ተከታዮች በዒሳ አምነው ዒሳን የመከተል ግዴታ አለባቸው። በዒሳ ያመኑም ደጋግ ሙስሊሞች ሲባሉ በዒሳ ማመንን ሳይቀበል በሙሳ ሃይማኖት ውስጥ እቆያለሁ የሚል ሰው ግን አማኝ አይደለም። ምክንያቱም ከአላህ በተላከ ነቢይ ማመንን ስላልተቀበለ ነው። ከዚያም አላህ የመልክተኞችን መጨረሻ ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) ከላከ በኋላ ሁሉም በርሳቸው የማመን ግዴታ አለባቸው። የመጨረሻውን መልዕክተኛ ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) የላከው ጌታ ያ ሙሳንና ዒሳን የላካቸው ጌታ ራሱ ነውና። ስለዚህ በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) መልእክት ክዶ "ሙሳን ወይም ዒሳን በመከተል ላይ ብቻ እቀጥላለሁ" የሚል ሰው አማኝ አይደለም።
አንድ ሰው ሙስሊሞችን አከብራለሁ ማለቱ ብቻውን በቂ አይደለም። በመጪው አለም ለመዳንም ምጽዋት መስጠትና ድሆችን መርዳት በቂ አይደለም። ይልቁንም አላህ ከርሱ ይህን ስራውን እንኳ እንዲቀበለው በአላህ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልክተኞቹ እና በመጨረሻው ቀን ማመን ግድ ይለዋል። ከሽርክ፣ በአላህ ከመካድ ፣ አላህ ያወረደውን ራዕይ ካለመቀበልና የመጨረሻውን ነቢይ የመሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) ነቢይነት ካለመቀበል የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለም። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) ተልዕኮ የሰሙ አይሁዶች፣ ክርስቲያኖች እና ሌሎችም በእርሳቸው ማመንንና ወደ እስልምና ሃይማኖት መግባትን ካልተቀበሉ ዘልአለማቸውን የጀሀነም እሳት ውስጥ ይሆናሉ። አላህ ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:
{إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ أُولَـٰئِكَ هُمْ شَرُّ الْبَرِيَّةِ} {እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡}[98: 6]
ለመላ የሰው ልጆች የተላለፈው የመጨረሻው ተልዕኮ ከአላህ ዘንድ የወረደ በመሆኑ ስለ እስልምናና ስለመጨረሻው ነብይ ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና) ተልዕኮ የሰማ ሰው ሁሉ በርሳቸው የማመን፣ ሸሪዓቸውን የመከተል እና ትእዛዛቸውን ታዞ ከከለከሉት የመቆጠብ ግዴታ አለበት። ስለዚህም የመጨረሻውን ተልዕኮ ሰምቶ የሚክድ አላህ ከእርሱ ምንንም አይቀበልም በመጪው ዓለምም ይቀጣዋል። የዚህም ማስረጃው የአላህ ንግግር ነው:
﴿وَمَن یَبۡتَغِ غَیۡرَ ٱلۡإِسۡلَـٰمِ دِینࣰا فَلَن یُقۡبَلَ مِنۡهُ وَهُوَ فِی ٱلۡـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلۡخَـٰسِرِینَ﴾ {ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው።}[3: 85]
አላህ እንዲህ ብሏል:(قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ) (የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡)(3: 64)
ሙስሊም ለመሆን የሚጠበቅብኝ ምንድን ነው?
ወደ እስልምና ለመግባት በእነዚህ ስድስት ማዕዘናት የማመን ግዴታ አለብህ:-
በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ማመን፤ እርሱ ፈጣሪ፣ ሲሳይ ሰጪ፣ አስተናባሪና የሁሉም ነገር ባለቤት መሆኑን ማመን፤ እርሱን የሚመስለውም ምንም ነገር የለም፣ ለርሱም ሚስትም ልጅም የለውም፣ እርሱ ብቻም ነው መመለክ የሚገባው ብሎ ማመን ነው።
በመላእክት ማመን፤ እነርሱ የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ባሪያዎች መሆናቸውን ማመን፤ ከብርሃን እንደፈጠራቸው፤ ከሥራቸውም መካከል አንዱ እነርሱ በነቢያቶች ላይ መለኮታዊ ራዕይ ይዘው እንደሚወርዱ ማመን ነው።
አላህ ለነቢያቱ ባወረደላቸው መጽሐፍት ባጠቃላይ (ከመበረዛቸው በፊት እንደ ተውራት እና ኢንጅል በመሳሰሉት) እና በመጨረሻው መጽሐፍ በተከበረው ቁርኣን ማመን፤
በሁሉም መልክተኞች ማመን፤ እንደ ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳ እና የመጨረሻው ነቢይ በሆኑት በሙሐመድ ማመን፤ መልክተኞቹ ሰው መሆናቸውንም ማመን ነው። አላህ በራዕይ አግዟቸዋል፤ እውነተኝነታቸውን የሚጠቁሙ ምልክቶችንና ተአምራትንም ሰጥቷቸዋል።
በመጨረሻው ቀን ማመን፤ ይህም አላህ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው (መላ ፍጥረታትን) የሚቀሰቅስበት፤ አላህም በፍጡራኑ መካከል የሚፈርድበት፤ አማኞችን ጀነት፣ ከሀዲዎችን ጀሀነም የሚያስገባበት ጊዜ ነው።
በቀደር ማመን: ይህም አላህ ያለፈውን እና ወደፊት የሚሆነውን ሁሉንም ነገር እንደሚያውቅ፤ አላህ ሁሉንም ነገር አውቆት ይህንንም እንደጻፈ፤ ሽቶትም ሁሉንም ነገር እንደፈጠረ ማመን ማለት ነው።
እስልምና የደስታ ጎዳና ነው።
እስልምና የዐረቦች ብቻ ሃይማኖት ሳይሆን የነቢያቶች ባጠቃላይ ሃይማኖት ነው።
እስልምና በዚህ ዓለም ውስጥ እውነተኛ ደስታን የሚያመጣ እና ከሞት በኋላ ባለው ዓለም ደግሞ ዘላለማዊ ፀጋን የሚያመጣ መንገድ ነው።
እስልምና የነፍስንና የሥጋን ፍላጎት ማሟላት እና ሁሉንም የሰው ልጅ ችግሮች መፍታት የሚችል ብቸኛ ሃይማኖት ነው።
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ:
{قَالَ اهْبِطَا مِنْهَا جَمِيعًا بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ فَإِمَّا يَأْتِيَنَّكُمْ مِنِّي هُدًى فَمَنِ اتَّبَعَ هُدَايَ فَلا يَضِلُّ وَلا يَشْقَى {አላቸው «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ሁላችሁም ከእርሷ ውረዱ ከእኔም የሆነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡وَمَنْ أَعْرَضَ عَنْ ذِكْرِي فَإِنَّ لَهُ مَعِيشَةً ضَنْكًا وَنَحْشُرُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَعْمَى ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡}[20:123,124]
ወደ እስልምና በመግባቴ ምን እጠቀማለሁ?
ወደ እስልምና መግባት በርካታ ትላልቅ ጥቅሞች አሉት። ከነርሱም መካከል:
የአሏህ ባርያ በመሆኑ በዚህ ዓለም ውስጥ ስኬት እና ክብርን ያጎናፅፈዋል። የአላህ ባሪያ ካልሆነ ግን የስሜታዊነት፣ የሰይጣን እና የፍላጎቱ ባሪያ ነው የሚሆነው።
የመጪው አለም ትልቁ ስኬት የሚባለው ከእሳት ቅጣት መዳንና ጀነት መግባት ፤ የአላህን ውዴታ መጎናፀፍና በጀነት ውስጥ መዘውተር ነው።
እነዚያ አላህ ጀነት የሚያስገባቸው ሞትም ይሁን ማንኛውም አይነት ህመም፣ ሀዘን፣ እርጅና ሳይነካቸው በዘውታሪ ተድላ ውስጥ ሆነው የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ ያገኛሉ።
በጀነት ውስጥ ዓይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ የሰው ልጅ አዕምሮ ውል ብሎበት የማያውቅ ተድላ አለ።
የዚህም ማስረጃው የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ንግግር ነው:﴿مَنۡ عَمِلَ صَـٰلِحࣰا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنࣱ فَلَنُحۡیِیَنَّهُۥ حَیَوٰةࣰ طَیِّبَةࣰۖ وَلَنَجۡزِیَنَّهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُوا۟ یَعۡمَلُونَ﴾ {ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን። ይሰሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።}[16: 97]
እስልምናን ባልቀበል ምን እከስራለሁ?
ሰው እስልምናን ካልተቀበለ ትልቁን እውቀት ይከስራል። ይህም አላህን ማወቅ እና ስለርሱ መገንዘብ ነው። በዚህ ዓለም ውስጥ ደህንነት እና መረጋጋትን የሚሰጠውንና በመጪው አለም ደግሞ ዘላለማዊ ደስታን የሚሰጠውን በአላህ የማመንንም ፀጋ ይነፈጋል።
አላህ ለሰዎች ያወረደውን ታላቁን መጽሐፍ ከማንበብ እና በዚህ ታላቅ መጽሐፍ ላይ ያለውን ከማመንም ይከስራል።
በትላልቅ ነቢያት ማመንንም ይከስራል። ልክ እንደዚሁ በትንሳኤ ቀን ጀነት ውስጥ ትላልቅ ነቢያቶችን መጎዳኘትንም እንደሚነፈገው ሁሉ ማለት ነው። ከሰይጣናት፣ ከወንጀለኞች እና ከጣዖቶች ጋር በመጎዳኘት በገሀነም እሳት ውስጥ ይሆናል። ምንኛ የከፉ መኖሪያውና ተጎራባቾች ናቸው!
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:
قُلْ إِنَّ الْخَاسِرِينَ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنْفُسَهُمْ وَأَهْلِيهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَلا ذَلِكَ هُوَ الْخُسْرَانُ الْمُبِينُ (15) {"ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሳኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልፅ ኪሳራ ነው።" በላቸው። (15)لَهُمْ مِنْ فَوْقِهِمْ ظُلَلٌ مِنَ النَّارِ وَمِنْ تَحْتِهِمْ ظُلَلٌ ذَلِكَ يُخَوِّفُ اللَّهُ بِهِ عِبَادَهُ يَا عِبَادِ فَاتَّقُونِ } . ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የሆኑ (ድርብርብ) ጥላዎች አልሏቸው፡፡ ከበታቻቸውም ጥላዎች አልሏቸው። ይህ አላህ ባሮቹን (እንዲጠነቀቁ) በእርሱ ያስፈራራበታል፡፡ «ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ፡፡»}[39: 15,16]
ውሳኔህን አታዘግይ!
ይህች ዓለም የመዘውተሪያ አገር አይደለችም .....
በዚህች አለም ያሉ ሁሉም ውበቶች ይሰወራሉ፤ ሁሉም ፍላጎቶችም ይጠፋሉ ......
ባሳለፍከው ነገር ሁሉ የምትተሳሰብበት ቀን መምጣቱ አይቀርም። እርሱም የትንሳኤ ቀን ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:{وَوُضِعَ الْكِتَابُ فَتَرَى الْمُجْرِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَا وَيْلَتَنَا مَالِ هَذَا الْكِتَابِ لاَ يُغَادِرُ صَغِيرَةً وَلاَ كَبِيرَةً إِلاَّ أَحْصَاهَا وَوَجَدُوا مَا عَمِلُوا حَاضِرًا وَلاَ يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا} {(ለሰው ሁሉ) መጽሐፉም ይቀርባል፡፡ ወዲያውም ከሓዲዎችን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ «ዋ ጥፋታችን! ለዚህ መጽሐፍ (ከሥራ) ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢኾን እንጂ የማይተወው ምን አለው» ይላሉም፡፡ የሰሩትንም ነገር ሁሉ ቀራቢ ኾኖ ያገኙታል፡፡ ጌታህም አንድንም አይበድልም፡፡}[18: 49]
ሙስሊም ያልሆነ ሰው መመለሻው ለዘለዓለም በጀሃነም እሳት ውስጥ እንደሆነ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ነግሮናል።
የትንሳኤ ቀን ክስረት እንደቀላል የሚታይ አይደለም። ይልቁኑም እጅግ በጣም አደገኛ ነገር ነው።{وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ } {ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡}[3: 85]
እስልምና አላህ ከርሱ ውጪ ያሉ ሃይማኖቶችን የማይቀበልበት ብቸኛው ሃይማኖት ነው።
አላህ እንደፈጠረን ሁሉ መመለሻችንም ወደርሱ ነው። ይህች አለም ለኛ ፈተና ነች።
እርግጠኛ መሆን ያለብህ ጉዳይ ቢኖር: ይህ ህይወት እንደ ህልም አጭር መሆኑን ... እና ማንም መቼ እንደሚሞት አለማወቁን ነው።
"እውነትን ያልተከተልከው ለምንድን ነው? የመጨረሻውን ነቢይ ለምን አልተከተልክም?" ብሎ ፈጣሪህ የትንሳኤ ቀን የጠየቀህ ጊዜ መልስህ ምን ይሆናል?
በእስልምና ክህደት የሚያስከትለውን መዘዝ አስጠንቅቆህና የከሓዲዎችም እጣ ፈንታ በጀሀነም ውስጥ ዘላለማዊ ጥፋት መሆኑን ነግሮህ ሳለ በትንሳኤ ቀን ለጌታህ ምን ትመልስለታለህ?
አላህ እንዲህ ብሏል:﴿وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ﴾ {እነዚያም (በመልክተኞቻችን) የካዱ በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡}[2: 39]. [2: 39]
እውነትን ትቶ አባቶቹንና አያቶቹን የተከተለ ሰው ምንም ተቀባይነት ያለው ምክንያት የለውም።
ብዙ ሰዎች የሚኖሩበትን አካባቢ ሁኔታ በመፍራት እስልምናን ሳይቀበሉ እንደሚቀሩ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ነግሮናል።
ብዙ ሰዎች እስልምናን የማይቀበሉት ከአባቶቻቸው የወረሱትን ወይም ከአካባቢያቸውና ከማህበረሰባቸው የተቀበሉትን እና የለመዱትን እምነታቸውን መለወጥ ስለማይፈልጉ ነው። ብዙዎቹ እስልምናን የማይቀበሉት የወረሱት ከንቱ የሆነ ወገንተኝነት እና ወግ አጥባቂነት ከልክሏቸው ነው።
እነዚህ ሁሉ ሰዎች ለዚህ ምንም ተቀባይነት ያለው ምክንያት የላቸውም። ስለዚህም አላህ ፊት ያለ ማስረጃ መቆማቸው አይቀርም።
አምላክ የለም ለሚል ሰው "የተወለድኩት አምላክ የለም ከሚል ቤተሰብ ውስጥ ስለሆነ ከሀዲ እንደሆንኩ እኖራለሁ።" ማለቱ ተቀባይነት ያለው ምክንያት አይሆንለትም። ይልቁንም አላህ የሰጠውን አእምሮ ተጠቅሞ የሰማይና የምድርን ታላቅነት እያሰላሰለ ይህ ጽንፈ ዓለም ፈጣሪ እንዳለው ይገነዘብ ዘንድ በአእምሮው ማሰብ ይገባዋል። ልክ እንደዚሁ አባቶቻቸውን በመከተል ድንጋዮችንና ጣዖታቶችን የሚያመልኩም ምንም ተቀባይነት ያለው ምክንያት የላቸውም፤ ይልቁንም እውነትን ፈልጎ እነዚህን ጥያቄዎች ራሱን መጠየቅ አለበት፡- የማይሰማኝን፣ የማያየኝን፣ ምንም የማይጠቅመኝን ግዑዝ ነገር እንዴት አመልከዋለሁ?!
ልክ እንደዚሁ አንድ ከንፁህ ተፈጥሮና ከአመክንዯዊ አስተሳሰብ ጋር በሚቃረኑ ነገሮች የሚያምን ክርስቲያንም ራሱን እንዲህ ብሎ መጠየቅ ይኖርበታል፡- "ጌታ ስለሌሎች ሰዎች ኃጢአት ብሎ እንዴት ምንም ሀጢዐት ያልሰራውን ልጁን ይገድላል?! ይህ ግፍ ነው! ሰዎችስ የጌታን ልጅ እንዴት ሰቅለው ሊገድሉት ቻሉ?! ጌታ ልጁን እንዲገድሉት ሳይፈቅድ የሰውን ልጅ ኃጢአት ይቅር ማለት አይችልምን?! ጌታ ለልጁ እንኳ መከላከል አይችልም?"
አይምሮው ጤነኛ የሆነ ሰው እውነትን መከተል እንጂ አባቶችንና አያቶችን በከንቱ መከተል የለበትም።
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:﴿وَإِذَا قِیلَ لَهُمۡ تَعَالَوۡا۟ إِلَىٰ مَاۤ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَإِلَى ٱلرَّسُولِ قَالُوا۟ حَسۡبُنَا مَا وَجَدۡنَا عَلَیۡهِ ءَابَاۤءَنَاۤۚ أَوَلَوۡ كَانَ ءَابَاۤؤُهُمۡ لَا یَعۡلَمُونَ شَیۡـࣰٔا وَلَا یَهۡتَدُونَ﴾ {ለእነርሱም አላህ ወደ አወረደውና ወደ መልክተኛው ኑ በተባሉ ጊዜ "አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበት ነገር ይበቃናል።" ይላሉ። አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና የማይመሩ ቢሆኑም (ይህንን ማለት ይበቃቸዋልን?!)}[5: 104]
እስልምናን መቀበል ቢፈልግም ነገር ግን ቤተሰቦቹ እንዳያስቸግሩት የሚፈራ ሰው ምን ማድረግ አለበት?
እስልምናን መቀበል ቢፈልግም በዙሪያው ያለውን አካባቢያዊ ሁኔታ የፈራ ሰው ራሱን ችሎ የሚወጣበትንና እስልምናውን ግልፅ የሚያደርግበት የተሻለ መንገድ አላህ እስኪያመቻችለት ድረስ እስልምናን ተቀብሎም እስልምናውን መደበቅ ይችላል።
ስለሆነም ወዲያውኑ እስልምናን መቀበሉ ግዴታህ ነው። ነገር ግን እስልምናን በመቀበልክ የምትጎዳ ከሆነ በዙሪያህ ላሉ ሰዎች የማሳወቅ ወይም ይፋ የማውጣት ግዴታ የለብህም።
እስልምናን ከተቀበልክ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሙስሊሞች ወንድም እንደምትሆን አውቀህ በአካባቢህ ካለ መስጊድ ወይም ኢስላማዊ ማእከል ጋር በመነጋገር ምክር እና እርዳታን መጠየቅ ትችላለህ። ይህም እነርሱን ደስተኛ ያደርጋቸዋል።
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:
{وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِب} {አላህን የሚፈራ ሰው ለርሱ መውጫን ያደርግለታል። ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል።}[65: 2,3]
ውድ አንባቢ ሆይ!
- ፀጋዎቹን ሁሉ የዋለልክን፣ በእናትህ ሆድ ውስጥ ፅንስ እያለህ ምግብ የሰጠህን እና አሁን የምትተነፍሰውን አየር የሰጠህን - ፈጣሪህን አላህ ማስደሰት ሰውን ከማስደሰት በላይ አስፈላጊ አይደለምን?
ለዚህች ዓለም እና ለመጪው ዓለም ስኬት ሲባል ሁሉንም ጊዜያዊ የህይወት ደስታዎችን መስዋዕት ማድረግ አይገባምን? እንዴታ! በአላህ እምላለሁ ይገባዋል!
ያሳለፍከው የህይወት መስመር የተሳሳተ መንገድህን ከማረም እና ትክክለኛውን ነገር ከማድረግ እንዲያግድህ አታድርግ።
ዛሬውኑ እውነተኛ አማኝ ሁን! እውነትን ከመከተል ሰይጣን እንዲያስቆምህ አትፍቀድ!
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል:
{يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمْ بُرْهَانٌ مِنْ رَبِّكُمْ وَأَنزلْنَا إِلَيْكُمْ نُورًا مُبِينًا (174) {እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥ አስረጅ መጣላችሁ፤ ወደእናንተም ገላጭ የሆነን ብርሃን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ (174)فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَاعْتَصَمُوا بِهِ فَسَيُدْخِلُهُمْ فِي رَحْمَةٍ مِنْهُ وَفَضْلٍ وَيَهْدِيهِمْ إِلَيْهِ صِرَاطًا مُسْتَقِيمًا (175) } እነዚያማ በአላህ ያመኑ በርሱም የተጠበቁ ከሱ በኾነው እዝነትና ችሮታ ውስጥ በእርግጥ ያስገባቸዋል፡፡ ወደእርሱም ቀጥተኛ መንገድን ይመራቸዋል፡፡} (175)[4: 174,175]
በህይወቶ ትልቁን ውሳኔ ለማድረግ ዝግጁ ነዎት?
ቀደም ተብሎ የተጠቀሰው ይህ ሁሉ አሳማኝ ከሆነልህ እና እውነቱንም ከልብህ ካወቅክ ሙስሊም ለመሆን የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰድ አለብህ። በህይወትህ ውስጥ የተሻለውን ውሳኔ እንድትወስን እገዛየን ትፈልጋለህን? ሙስሊም መሆን በምትችልበት መንገድ ላይ ጥቆማየን ትፈልጋለህን?
ወንጀልህ ወደ እስልምና እንዳትገባ ሊከለክልህ አይገባም። አንድ ሰው እስልምናን ከተቀበለ እና ወደ ፈጣሪው ከተፀፀተ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት የነበረውን ኃጢአቱን ሁሉ ይቅር እንደሚለው አላህ በቁርአኑ ውስጥ ነግሮናል፤ እስልምናንም ተቀብለህ እንኳ ስህተት ላይ ብትወድቅ አንተ ሰው እንጂ የማይሳሳቱ መላእክት ስላልሆንክ አንዳንድ ኃጢአቶችን መስራትህ ተፈጥሯዊ ነው። ይልቅ ከኛ የሚጠበቀው አላህን ምህረትን መለመን እና ተፀፅተን ወደርሱ መመለስ ነው። አላህም ሀቅን ፈጥነህ መቀበልህን፣ ወደ እስልምና መግባትህን፣ ሸሃዳን መመስከርህን አይቶ ሌሎች ወንጀሎችን እንድትተውም ይረዳሀል። ወደ አላህ የሚዞር ሰው እና እውነትን የሚከተል ሰውን አላህ ወደ ተጨማሪ መልካም ነገር ይመራዋልና። ስለዚህ አሁኑኑ ወደ እስልምና ከመግባት አታቅማማ!
የዚህም ማስረጃው ተከታዩ የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ንግግር ነው:﴿قُل لِّلَّذِینَ كَفَرُوۤا۟ إِن یَنتَهُوا۟ یُغۡفَرۡ لَهُم مَّا قَدۡ سَلَفَ﴾ {ለነዚያ ለካዱት በላቸው:- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ስራ) ምህረት ይደረግላቸዋል።}[8: 38]
ሙስሊም ለመሆን ምን ማድረግ ይጠበቅብኛል?
ወደ እስልምና መግባት ቀላል ጉዳይ ነው። የተለየ ሃይማኖታዊ ስርአትም ይሁን መግለጫ ወይም የማንንም መገኘት አይጠይቅም። ትርጉማቸውን አውቆና አምኖባቸው (ተከታዮቹን) ሁለቱን የምስክርነት ቃሎች መናገር ብቻ ነው የሚጠበቅበት: ይህም "አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" ማለት ነው። (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ) ማለት ነው። በዐረብኛ ቋንቋ መናገር ከገራልህ መልካም ነው። ይህ ከከበደህ ግን በቋንቋህ መናገርህ ራሱ በቂ ነው። በዚህም ሙስሊም ትሆናለህ። ቀጥሎ የዚህ አለም ደስታህና የመጪው አለም መዳኛህ ምንጭ የሚሆነውን ሃይማኖትህን መማር ነው ያለብህ።
ስለ እስልምና የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህን ድህረ ገጽ እንድትጎበኝ እመክራለሁ:
የቅዱስ ቁርኣንን ትርጉሞች በተለያዩ ቋንቋዎች ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ ፡-
እስልምናን እንዴት እንደሚተገብሩ ለማወቅ ይህን ድህረ ገጽ እንዲጎበኙ እንመክራለን፡-
ማን ነው የፈጠረኝ? ለምንስ ፈጠረኝ?ሁሉም ነገር ፈጣሪ እንዳለ ይጠቁማል
ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው ጌታ ያሉት ባህሪያት
የምናመልከው ጌታችን መገለጫዎቹ የግድ ምሉዕ ባህሪ ሊሆኑ ይገባል።
ፈጣሪ ያለ መለኮታዊ ራዕይ ሊተወን ይችላል ተብሎ ይታሰባል?
ብዙ መልክተኞች የተላኩበት ምክንያት ምንድን ነው?
ማንኛውም ግለሰብ በሁሉም መልክተኞች ካላመነ አማኝ አይሆንም።
ሙስሊሞች በኢየሱስ (የአላህ ሰላም ይስፈንበትና) ዙሪያ ምንድን ነው የሚያምኑት?
እውነትን ትቶ አባቶቹንና አያቶቹን የተከተለ ሰው ምንም ተቀባይነት ያለው ምክንያት የለውም።
እስልምናን መቀበል ቢፈልግም ነገር ግን ቤተሰቦቹ እንዳያስቸግሩት የሚፈራ ሰው ምን ማድረግ አለበት?